በዘንድሮው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ 233 ቢሊዮን ብር ግብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 96.5 % ማሳካት ተችሏል

በዘንድሮው በጀት ዓመት 241‌.4 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ሲሆን 233 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 96.5 % ማሳካት ተችሏል ሲሉ ከንቲባ አድነች አቤቤ ተናገሩ::

ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት  83.3 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ወይም 45 በመቶ እድገት በከተማዋ ገቢ ላይ እድገት ያሳየ ነው። ያልተሰበሰበው 8 ቢሊዮን ብር ከእርዳታ እና ብድር ይገኛል ተብሎ በተጨማሪ በጀት የታወጀ ነበር ብለዋል።

ለውጥና እድገት በራስ አቅም ሲሆን  መሰረቱ ሰፊ፤ ምሰሶውም ጠንካራ ይሆናል።

"ውድ የከተማችን ነዋሪዎች፤ ውድ ግብር ከፋዮቻችን፤ ውድ የገቢዎች ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች እንዲሁም ውድ ባለድርሻ አካላት  ለተገኘዉ ስኬት በራሴ እና በከተማው አስተዳደሩ እንዲሁም በከተማችን ነዋሪዎች ስም አመሰግናለሁ።"

"ነገም አቅማችን እናንተው ናችሁና፤ ችግሮችን እያረምን በራስ አቅም፣ በትብብር፣ በጠንካራ እምነት እና የስራ ባህል እየመራናት የከተማችን እድገት ይቀጥላል" ብለዋል::