በቴክሳስ በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 43 ደረሰ


በአሜሪካ ማዕከላዊ ቴክሳስ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የሟቾች  ቁጥር 43 መድረሱን የአካባቢው ባለስልጣናት ገለጹ።

ከሟቾቹ መካከል 15 የሚሆኑት ህጻናት እንደሆኑ ተገልጿል።

የነፍስ አድን ሰራተኞች በጎርፉ ሳቢያ የደረሱበት ያልታወቁ ነዋሪዎችን ለመፈለግ እየሞከሩ ስለመሆኑ ሮይተርስ ዘግቧል። 

አንዳንድ ብዙሃን መገናኛዎች ደግሞ የሟቾች ቁጥር ከ50 ስለመሻገሩ ዘግበዋል።

ከአደጋው ቦታ ባሻገር ኬር በተባለ አካባቢ ያሉ ቦታዎች በጎርፍ የተጎዱ በመሆናቸው የተጎጂዎች ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችል ባለስልጣናት ተናግረዋል። 

የትራቪስ አካባቢ ባለስልጣን እንዳሉት በጎርፍ አደጋ 4 ሰዎች መሞታቸውንና 13ቱ የደረሱበት ያልታወቀ መሆኑንም ገልፀዋል።